top of page

                              Welcome to Our Community.

At the heart of Cottage Grove, Woodbury and saint Paul Park area the Ethiopian and Eritrean community is more than just a group of neighbors—we are a family. Whether you have lived here for decades or have just arrived, this is your space to connect, celebrate, and grow.

​​​

Cottage Grove, Woodbury and Saint Paul Park area Ethiopian and Eritrean Community

We take pride in serving the Ethiopian and Eritrean families living
in Cottage Grove and the surrounding South Washington County region.

እንኳን ወደ ቤታችሁ፣ ወደ ማህበረሰባችን በደህና መጣችሁ​​​​

​​

eth-new-year-678x381.jpg
Our MISSION

The Cottage Grove, Woodbury and Saint Paul Park area Ethiopian and Eritrean Community (CGEEC) is focused on improving the of life for individuals and families by providing extensive support services, fostering pride, and promoting self-sufficiency. We are dedicated to empowering the community by ensuring access to education, healthcare, employment resources, and social services, while nurturing connections among various cultures and communities.

  Together we can make a deference

LATEST NEWS

እንኳን ለብርሃነ እንቁጣጣሽ እና ለ፳፻፲፱ (2019) አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ማህበረሰብ አባላት በሙሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የመደጋገፍ ይሁንልን። ያለፈው ዓመት ውጣ ውረድ አልፎ አዲሱ ዓመት አዲስ ተስፋ፣ አዲስ እድል እና ሙሉ በረከት ይዞልን እንዲመጣ እንመኛለን።

መልካም አዲስ ዓመት!

SUBSCRIBE

Subscribe to Our Newsletter

maxresdefault.jpg
Colorful Spheres

Our community is a place where people from all backgrounds come together to share their interests and passions. We strive to create a welcoming and inclusive space for all who join us.

latest news
Ethiopian-Food.jpg

​                  ጤና

በማኅበረሰባችን ውስጥ የጤናማ አኗኗርና የምግብ አበላል ባህልን ማሳደግ

                       የተወደዳችሁ የማኅበረሰባችን አባላት፣

ጤና የህይወታችን መሠረትና ለቤተሰቦቻችን መስጠት የምንችለው ትልቁ ሀብት ነው። ልጆቻችን እኛ የምናደርገውን እያዩና እየተከተሉ ስለሚያድጉ፣ ዛሬ በቤታችን የምንተክለው የጤና አኗኗር ነገ የልጆቻችንን ብሩህ ተስፋ ይወስነዋል። እንደ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ባህላችንን እና የምግብ አሰራራችንን ጠብቀን በመኖር ሂደት ውስጥ፣ ጥቂት ቀላል ማስተካከያዎችን በማድረግ የቤተሰቦቻችንን ጤና በከፍተኛ ደረጃ መጠበቅ እንችላለን።

1. ከልክ ያለፈ ዘይትና ስብን መቀነስ

ባህላዊ ምግቦቻችን (እንደ ወጥና ጥብስ ያሉ) እጅግ ጣፋጭ ቢሆኑም፣ በምግብ አሰራር ወቅት የምንጠቀመው ዘይት ወይም ቅቤ ከልክ በላይ ሲሆን ለደም ግፊት፣ ለልብ ህመም እና ለስኳር በሽታ አጋላጭ ይሆናል።

 መፍትሔ፡ ወጥ ሲሰራ ዘይት በጭልፋ ከመድፋት ይልቅ በስpoon በመለካት መቀነስ።

 ጥብስና አልጫ ምግቦችን በትንሽ ዘይት በመስራት የእውነተኛውን ምግብ ጣዕም መለማመድ።

2. ከልክ በላይ አብስሎ ማውጣት    (Overcooking)

ምግቦችን (በተለይም አትክልቶችን) ከልክ በላይ አብስሎ ማውጣት በውስጣቸው የሚገኙትን ዋና ዋና ቪታሚኖችና ማዕድናት ያጠፋቸዋል።

 መፍትሔ፡ አትክልቶች (እንደ ጐመን፣ ካሮት፣ ጥቀስ ጐመን) ሙሉ በሙሉ አልቀው ሳይጠፉና ለስልሰው ሳይበላሹ በከፊል አብስሎ መመገብ።

3. አትክልትና ፍራፍሬን የዘወትር ምግብ ማድረግ

ከእንጀራና በሬ/በግ ስጋ በተጨማሪ በየቀኑ ሳህናችን ላይ ሰላጣ፣ ካሮት፣ ብሮኮሊ እና ትኩስ ፍራፍሬዎች መኖር አለባቸው።

 መፍትሔ፡ ከምግብ በፊት ወይም ከምግብ ጋር አብሮ ትኩስ ሰላጣ የመመገብ ልምድ ማዳበር።

4. የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ (ከቤተሰብ ጋር)

ጤናማ ምግብ ብቻውን ሙሉ አይሆንም፤ ሰውነታችን መላወስ አለበት።

 መፍትሔ፡ ምሽት ላይ ከቤተሰብ ጋር በእግር መጓዝ፣ ከልጆች ጋር በፓርክ መጫወት ወይም ቅዳሜና እሁድ የጋራ እንቅስቃሴ ማድረግ።

 ልጆቻችን ስክሪን (ቲቪ/ስልክ) ላይ ከሚያጠፉት ጊዜ ይልቅ ከእኛ ጋር የሚንቀሳቀሱበትን መንገድ ማመቻቸት።

ልጆቻችን የእኛ መስታወት ናቸው!

ልጆቻችን እኛ የምንበላውን ይበላሉ፣ የምናደርገውን ያደርጋሉ። እኛ ዛሬ አትክልት ስንመገብ፣ ዘይት ስንቀንስ እና ስንቀሳቀስ ሲያዩ፣ እነሱም ያንን የጤናማ ህይወት መንገድ ይከተላሉ።

ዛሬ በቤታችን ከምናዘጋጀው ምግብ ጀምረን ትናንሽ ለውጦችን በማድረግ ለቤተሰባችንና ለወደፊቱ ትውልዳችን ጤናማ መንገድ እንክፈት!

Contact Us

500 Terry Francine Street

San Francisco, CA 94158

info@mysite.com

Connect with us
Subscribe

CGEE 

© 2026 Cottage Grove Ethiopian and Eritrean community 

bottom of page